- አንዲት ነፍሰጡር እናት ቅሪት ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ የምትወስደው ምግብ የተመጣጠነ መሆን አለበት፡፡
- እናት ይህን ድርሻዋን በአግባቡ ለመወጣት የተመጣጠነ ምግብ የመመገብ ባህሏን ማዳበር ይገባታል። ይኼም
- የእዚህ ዋነኛ ምክንያት ደግሞ የተመጣጠነ ምግብ እያገኘ ያደገ ሕፃን በአዕምሮውና በአካሉ የበለፀገ መሆኑ ነው፡፡ በተቃራኒው የተመጣጠነ ምግብ ያላገኘ ልጅ ለሰውነት መቀንጨር ችግር ይጋለጣል፡፡
መቀንጨር ያጋጠመው ልጅ አካላዊ እድገቱ የሚገታ ሲሆን ክብደቱም አነስተኛ ነው፡፡ ተክለሰውነቱም ከዕድሜው በታች ያነሰ ሆኖ ይታያል፡፡ በተለይ ጉልበት በሚጠይቅ ሥራ ላይም ደካማ ስለሚሆን ምርታማነቱ ይቀንሳል። ነገሮችን ቶሎ ለመቀበልና ለመፍጠር ያለው ብቃት አናሳ ስለሚሆን በትምህርቱም ወደኋላ ይቀራል፡፡
በተመጣጠነ ምግብ እጥረት የሚከሰተውን የመቀንጨር ችግር ቀድሞ በመከላከል ካልሆነ በቀር በሕክምና የሚገኘው መፍትሄ ከሃያ በመቶ አይበልጥም፡፡
የተሻለውና ብቸኛው አማራጭ በእርሻ የሚገኝ ሰብል፣ የጓሮ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ እንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ፣ ዓሣና የመሳሰሉትን ገንቢ ምግቦች በተመጣጠነ ሁኔታ መጠቀም ነው፡፡
በመውለድ ክልል ውስጥ የምትገኝ ሴት ጽንስ ከመያዟ በፊትም ሆነ በእርግዝና ጊዜዋ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ይኖርባታል።
ጤናማ ፅንስና የተመጣጠነ ምግብ
ለጤናማ እርግዝና እና ጤናማ ፅንስ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው። የተመጣጠኑ ምግብ ዓይነቶች ሊገኙ የሚችሉት ፡-
- ፕሮቲን (ሰውነት ገንቢ):– ስጋ፣ ዓሳ፣ እንቁላል፣ የወተት ውጤቶች የመሳሰሉት፡፡
- ቅባት :- ቅቤ፣ ዘይት፣ ማርጋሪን/የዳቦ ቅባት/፣ የወተት ውጤቶች፡፡
- ኃይልና ሙቀት ሰጪ ፡-ዳቦ፣ፓሰታ፣ ድንች፣ ሩዝ፣ በቆሎ፣የአዝዕርት ውጤቶችና የመሳሰሉት፡፡
- ቫይታሚኖች ፍራፍሬ፣ አትክልቶች፣ ፎሊክ አሲድ/ቫይታሚን ቢ9 በመጀመሪያዎቹ ሶስት የእርግዝና ወራት ከጥራጥሬዎች፣ ፍራፍሬዎች፣ ብርትኳን ጭማቂ፣ ሩዝ እና ከመሳሰሉት ማግኘት ይቻላል፡፡