የወሊድ ዕቅድ

የወሊድ ዕቅድ ማውጣት በወሊድ ጊዜ ብዙ ሁኔታዎችን በምትፈልጓቸው መልኩ ለማመቻቸት ይረዳችኋል።

የወሊድ ዕቅዳችሁን በምታወጡበት ጊዜ ልታስቧቸው ከሚገቡ ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ፡-

  • ከጤና ባለሙያ ጋር በመሆን የት ለመውለድ እንዳሰባችሁ ማቀድ ያስፈልጋል።
  • በቅርብ የሚገኘው የጤና ማዕከል ወይም ሆስፒታል የት እንደሚገኝ ማወቁ ጠቃሚ ነው።
  • ከጤና ባለሙያ ጋር በመሆን የት ለመውለድ እንዳሰባችሁ ማቀድ ያስፈልጋል።
  • በቅርብ የሚገኘው የጤና ማዕከል ወይም ሆስፒታል የት እንደሚገኝ ማወቁ ጠቃሚ ነው።
  • ለመጓጓዣና ለተለያዩ የሕክምና ወጪዎች ገንዘብ ማዘጋጀት
  • መጓጓዣ በቀላሉ የሚገኝበትን መንገድ ማመቻቸት
  • በወሊድ ወቅት ሊረዳ የሚችል የቤተሰብ አባል በቅርብ እንዲኖር ማድረግ
  • ለህፃኑ የሚሆን ልብሶችና የመኝታ ቦታ ማመቻቸት
  • ከወሊድ በኋላ እናቲቱ የምትመገበውን ምግብ ቀደም ብሎ ማሰናዳት፡፡

የት እና ማን እንደሚያዋልድሽ ማወቅ

  • ለሕክምና እና ለትራንስፖርት ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ማቀድ በእርግዝና ወቅትም ሆነ ከእርግዝና በኋላ ወላጆች የተለያዩ ወጪዎች ይኖሩባቸዋል። ስለዚህ በእርግዝና ጊዜ በየወሩ የተወሰነ ገንዘብ ተቀማጭ ማድረጉ አስፈላጊ ነው።
  • በተጨማሪም በእርግዝና ወቅት ወደ ህክምና ቦታ ለመሄድ እንዲሁም ምጥ በሚመጣበት ጊዜ ለመውለድ ወደታቀደበት ተቋም ለመሄድ መጓጓዣ ቀድሞ ማዘጋጀት ያስፈልጋል።

ለምሳሌ፡- ታክሲ አናግሮ የሹፌሩን ስልክ መያዝ ወይም መኪና ያለውን ዘመድ አናግሮ ተዘጋጅቶ
መጠበቅ በጣም አስፈላጊ ነው።