ቅድመ ወሊድ ሕክምና

አንዲት ሴት ነፍሰጡር መሆኗን ካረጋገጠች ቡኋላ ከመውለዷ በፊት ቢያንስ አራት ጊዜ ወደ ጤናተቋም በመሄድ የቅድመ ወሊድ ምርመራ ማግኘት ይኖርባታል። የእርግዝና ምልክቶችን እንዳየች ወዲያውኑ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ተጨማሪ የህክምና ክትትል ማግኘት ይኖርባታል።

አንዲት ነፍሰ ጡር ከትዳር አጋርዋጋር ሆና ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ተገቢውን የቅድመወ ሊድክትትል ማድረጓ ለራሷም ሆነ በማህፀኗ ውስጥ ላለው ህፃን ጤንነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው።

እርግዝና በዘመናዊ ህይዎት ታስቦ እና ታቅዶ የሚመጣ የተፈጥሮ ሂደት  ነዉ። ማንኛዉም ጥንዶች እርግዝናን ቀድመዉ ማቀድ፣ የህክምና ክትትል ምርመራዎችን ማድረግ፣ ቅድመ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለባቸው።

ቅድመ ምርመራዎች እና እቅዶች ጤናማ እርግዝና እንዲሆን ይረዳሉ። በተጨማሪም ጥንዶች ልጅ ከመፈለጋቸዉ በፊት የተለያዩ የእርግዝና መከላከያዎችን ሲወስዱ ከነበሩ ለማርገዝ መከላከያዉን መቼ በማቆም እና ምን ማድረግ እንዳለባቸዉ ከሀኪም ጋር መመካከር አስፈላጊ ነዉ።

አንዳንድ ሴቶች የእርግዝና መከላከያ ከወሰዱ ቡኋላ ለመጸነስ ይቸገራሉ። በተለይ በመርፌ የሚወሰድ መከላከያ እና ሌሎች ሆርሞን ያላቸዉ መከላከያዎች ቶሎ ከሰዉነት ላይጠፉ ስለሚችሉ ያንን ሲወስዱ የነበሩ ሴቶች በፈለጉት ጊዜ የመጸነስ እድላቸዉ ጠባብ ነዉ። እስከ 1 አመትም ሊዘገይ ይችላል።

ቅድመ ሁኔታዎች ዉስጥ  የሚመደቡ  ሴቷ የምትወስደዉ  መድሃኒት  ለተለያዩ በሽታዎች ሊሆን ይችላል እነዚህን መድሃኒቶች ከእርግዝና ጋር እንደሚሄዱ እና መቀየር ካለባት ከሀኪሟ ጋር ብትነጋገርበት ለጤናዋም ለሚረገዘዉ ልጅም አስፈላጊ ነዉ።

በመጀመሪያ ቅድመ እርግዝና  ምርመራ ማድረግ ሁሉንም ከእርግዝና ጋር የሚመጡ በሽታዎችን ይከላከላል ማለት አይደለም ። አንዳንድ ችግሮች እርግዝና ከተፈጠረ ቡኋላ የሚመጡ ናቸዉ።

ሌላዉ ቅድመ እርግዝና ምርመራ ለሲጋራ እና የመጠጥ ሱስ ላለባቸዉ ጥንዶች ማርገዝ እንዲችሉ ወይም ከተረገዘ ቡኋላ ሱሶቹ ጽንሱ ላይ ከሚያመጣዉ አሉታዊ ተጽኖዎች እንዲከላከሉ ይረዳል። ስለዚህም አንዳንድ ሱሶችን ቀድመዉ ማቆም ይችላሉ።

የመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ጊዜያቶች የሚባሉት ጽንሱ ከተፈጠረ እስከ 12ኛዉ ሳምንት ያለዉ ጊዜ ነዉ።