ድንገተኛ

ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ

ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ኤሜርጄንሲ ኮንትራሴፕቲቭ የወሊድ መቆጣጠርያ ሲሆን ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ የሚፈጠረውን እርግዝና ለመከላከል ይወሰዳል። ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያን ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ ወዲያው ወይም በ 120 ሰዓታት ውስጥ መጠቀም ይችላሉ።

ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እንክብሎች ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት በተፈፀመ በ120 ሰዓታት ውስጥ ወይም 5 ቀን በአፍ መወሰድ አለባቸው ይላሉ ባለሞያዎች፡፡

መከላከያዎቹን ለመውሰድ መዘግየት እርግዝና ሊያጋጥም የሚችልበትን ሁኔታ ይበልጥ እንዲጨምር ያደርጋል።  ቀኖች እየገፉ በሄዱ ቁጥር ግን እርግዝናን የመከላከል አቅሙ እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ ስለዚህ ወዲያውኑ መውሰድ ይመከራል፡፡

የወሊድ መቆጣጠርያዎ እንደማይሰራ፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ ኮንዶሙ እንደተበጠሰ፣ በወርሀዊ ዑደት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የወሊድ መቆጣጠርያ ኪኒኖች እንዳልወሰዱ ወይም የግብረ ስጋ ግንኙነት ተደፍረው እንዳደረጉ ካሰቡ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ እርግዝናን እንጅ ሌሎችን የአባላዘር በሽታዎችን ሊከላከል ስለማይችል እንደስያሜው ሁሉ አንዲት ሴት ድንገተኛ የእርግዝና ስጋት ውስጥ ስትገባ ብቻ ልትጠቀመው የሚገባ ነው፡፡

ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እርግዝና እንዳይከሰት ያደርጋል። ነገር ግን ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ልክ እንደ ኪኒን ወይም ኮንዶሞች ከግብረ ስጋ ግንኙነት በፊት ወይም በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት እንደሚወሰደው የወሊድ መቆጣጠርያ ውጤታማ አይደለም። ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያን እርግዝናን ለመከላከል እንደ ብቸኛ መከላከያ አይጠቀሙ። በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ወይም ከኤች አይ ቪ ኤድስን አይከላከልም።

ድንገተኛ የወሊድ መቆጣጠርያ በኪኒን  ወይም  በማህፀን ውስጥ በሚቀበር መሳርያ (አይዩዲ) መዳብ መልክ ይገኛል። ከልቅ ግብረ ስጋ ግንኙነት በ 120 ሰዓታት ውስጥ ኪኒኖቹ መወሰድ ወይም በማህፀን ውስጥ የሚቀበርረው መሳርያ (አይዩዲ) መከተት ይኖርባቸዋል።

ያልተጠበቀ ወሲባዊ ግንኙነትን፣ ሌላ የእርግዝና መከላከያዎች አስተማማኝነት በሚያጠራጥርበት ጊዜ ወይንም መደፈርን ተከትሎ ከሚወሰዱ የተለያዩ የእርግዝና መከላከያ መንገዶች መካከል የአስቸኳይ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ እንክብሎች የሚባሉት ይገኙበታል። እነዚህ እንክብሎች ግንኑነት በተደረገ በ 120 ሰዓታት ውስጥ መወሰድ ሲገባቸው የሚወሰዱበት መጠን እንደ ኬሚካል ይዞታቸው ይለያያል።

መከላከያዎቹን ለመውሰድ መዘግየት እርግዝና ሊያጋጥም የሚችልበትን ሁኔታ ይበልጥ እንዲጨምር ያደርጋል።