ማቋረጥ

የእርግዝና መከላከያ – ማቋረጥ

ይህ ዘዴ ወንዱ ብልቱን ከሴቷ ብልት ውስጥ ከመርጨቱ በፊት ማውጣትን ይጠይቃል። ይህን ዘዴ ሊጠቀሙ የሚችሉት ሌላ ዘዴ ከሌለ ነው።

በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ሊከላከል የማይችል እና በወንዱ በኩል እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ ራስን መቆጣጠር እና ልምድን ይጠይቃል።

ይህ ዘዴ የማይታመን እና በግምት ከ18-19% ያለመስራት እድል አለው። ማንኛውም የእርግዝና ምልክት ካጋጠመዎት የእርግዝና መጣራት ማድረግ ይገባዎታል።