መታቀብ

መታቀብ – የእርግዝና መከላከያ

መታቀብ ማለት የግብረ ስጋ ግንኙነት አለማድረግ ነው። ከግብረ ስጋ ግንኙነት ከታቀቡ አያረግዙም።

በህይወትዎ ውስጥ የሆነ ጊዜ የግብረ ስጋ ግንኙነት ላለማድረግ ሊወስኑ ይችላሉ። መታቀብን በየቀኑ ምርጫዎ የሚያደርጉት ነው። መታቀብን የመረጡት ለምን እንደሆነ ለራስዎ ማስታወስ ይኖርብዎታል፣  ስለሚመጡት አደጋዎች ያስቡ፣ ለግብረ ስጋ ግንኙነት የሚያነሳሱ ሁኔታዎች በሚኖሩበት ወቅት ውሳኔዎን በድጋሚ አይገምግሙ- በንፁህ አይምሮ ማሰብ እስከሚችሉ ድረስ በውሳኔዎ ይፅኑ።

መታቀብ ለምን እና ለማን?

  • ሰዎች እርግዝናን ለመከላከል
  • በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል
  • ለግብረ ስጋ ግንኙነት ዝግጁ እስከሚሆኑ ድረስ ለመጠበቅ
  • ትክክለኛ አጋራቸውን እስከሚያገኙ ድረስ ለመጠበቅ
  • ግብረ ስጋ ግንኙነት ሳይፈፅሙ ከፍቅር አጋራቸው ጋር ለመደሰት
  • ትምህርት፣ ስራ ወይም ተጨማሪ ስራዎች ላይ ለማተኮር

  • ግላዊነትን፣ ስነምግባር ወይም ሀይማኖታዊ አመለካከትን እና እሴትን ለመጠበቅ
  • መለያየትን ለማቆም
  • ከአጋር ሞት ለመፈወስ
  • በበሽታ ወይም በወረርሽኝ ወቅት የህክምና ትዕዛዝን ለመከታተል  መታቀብን ይመርጣሉ።

ማንኛውም ሴት ወይም ወንድ ከግብረስጋ ግንኙነት ጨዋታ ሊታቀብ ይችላል። ብዙ ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ በተለያዩ ጊዜያቶች ይታቀባሉ። አንዳንዶች ከግብረስጋ ግንኙነት ጨዋታ በህይወታቸው ውስጥ ለረጅም ጊዜያቶች መታቀብን ሊመርጡ ይችላሉ።

ጠቀሜታዎች

በመታቀብ ምንም አይነት የጤና ችግሮች የማይኖሩ ሲሆን ነፃ ነው። ብልትዎ ከአጋርዎ ብልት ጋር ካልተነካካ በስተቀር የማያረግዙ ሲሆን በግብረ ስጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች አይያዙም።

ጉዳቶች

ሀሳብዎን ከቀየሩ እና የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ ከወሰኑ፣ መታቀብ ምንም አይነት መከላከያ አያሰጥም። ሌላ የወሊድ መቆጣጠርያ ዘዴ በቅርበት ሊኖርዎት ይገባል።

ያስታውሱ፤ የግብረ ስጋ ግንኙነት ባያደርጉም በግብረ ስጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች ሊያዙ ይችላሉ።

በአፍ የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ ወይም የእርስ በእርስ የቆዳ ንክኪ፣ ለምሳሌ  የእያንዳንዳቸውን ብልት በማሻሸት እና በመደባበስ ሊያዙ ይችላሉ።

ለማርገዝ ካቀዱ፡ በቀላሉ መታቀብን ማቆም ነው። ወዲያው ለማርገዝ መሞከር ይችላሉ።